የአማርኛ ፊደል የሚባል የለም! ይህ ‘’የግዕዝ ፊደል ነዉ’’::

Articles

[ምንጭ:- ከOromia-My Country ፌስቡክ የተወሰደ]

ግዕዝ ‘አግዓዘ’ ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ‘’ነፃ አወጣ’’ ማለት ነዉ፡፡ የግዕዝ ባለቤቶች ‘’አግዓዝያን’’ ናቸዉ! አግዓዝያን ‘አግዓዘ’ ከሚል የግዕዝ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ነፃ አዉጭዎች ማለት ነዉ፡፡ አግዓዝያን ተብሎ የሚጠሩ ተጋሩ/ትግራይና ከፊል  ኤርትራኖች ናቸዉ!!!

ዘብሔረ አግዓዝያን ሲሉ ይጠሩታል!!! ለዚህ ማሳያ ደግሞ ትግራይ ጥንት ስሟ አግዓዝያን ተብላ ትጠራ ነበር፡፡ በፈሪሳዉያኑ የህዝቡ ቆራጥነትና ጀግንነት አይተዉ አድናቆታቸዉ ሲገልፁ Age’azians are Tigers! ይሉ ነበር፡፡ Tigers ማለት ነብሮች ሲሉ ነዉ፡፡ ካዛ ከ አግዓዝያን ወደ ተጋሩ ተቀየረ፡፡

ታድያ የግዕዙ ፊደል እንዴት የአማርኛ ፊደል ተባለ ይሉኝ እንደሆነ ሁሉም የኛ የሚል በሽታ የያዛቸዉ ወራሪዎች በግድ ሊወስዱት ስለፈለጉ እንጂ የአግዓዝያን ነዉ፡፡

ለዚህ ደግሞ የታሪክና የቅርስ ማማ የሆነቹ ባለ 3000 ሺ ዓመት የታሪክ ማህደር አክሱምን ሂደዉ ማየት ይችላሉ! ሐዉልቷና የቤተክርስትያኑ ግንብ ሳይቀር ግዕዝን ይናገራሉ!

እና የአማርኛ ፊደላት እንዴት ተባለ ካላችሁኝ የተበታተነ የወይጦ፤ የቅማንት፤ የአገዉ፤ የወሎ…. አንድ ላይ አሰባስቦ አማራ የሚባል ብሔር ያዋቀረዉ ወያኔ ገና የ27 ዓመት ብሔር ነዉ እላለሁ!

ግዕዝ ግን አማራነት ሳይኖር ከጥንት ጀምሮ በአገልግሎት የነበረ ነዉ!!! ስለዚህ ስሙ የግዕዝ ፊደል ነዉ ተብሎ የሚጠራዉ፡፡

እንድያ ከሆነማ እነሱ በግዕዝ ስለፃፉ የአማርኛ ፊደል ነዉ ካሉ እኛ የትግርኛ ፊደል ነዉ እንላለን ማለታቸዉ ነዉ፡፡ አማርኛና ትግርኛ ግን ከግዕዝ ቋንቋ የተፈጠሩ ናቸዉ ፡፡ ይህ መራራ ሓቅ አይደበቅም!!! ስለዚ የግዕዝ ቋንቋ ከነፊደሉ ነበር ማለት ነዉ፡፡ ዋናዉ ግዕዝ መቦቆሉ ከአግዓዝያን በአክሱም መሆኑ ልናቀዉ ይገባል! የግዕዝ ፊደል መሆኑ ግዕዝ ደግሞ የአግዓዝያን መሆኑና የአማርኛ አለመሆኑ ስነግራቹ ይህ ጦፍቶን ነዉ ልትሉ ይሆናል::

ግን የአማራ ነዉ የሚል መንጋ ስለተነሳ የግድ ማስረዳት ስላለብኝ ነዉ፡፡ የፊደላቱ ትርጉም ከሊቃዉንቱ ያገኘሁት ልንገራቹ፡፡ እናተም አንብባቹ  ስትጨርሱ ለሌላዉ ሼር በማድረግ መስክሩ፡፡ ትግራይ ኩሕሎ ነኝ ከብሔረ አግዓዝያን፡፡

የፊደላቱ ትርጓሜ በሊቃውንት የሚደንቅ! … ስንቶቻችን እናውቃለን?

እነሆ ትርጉማቸው …

ሀ ማለት ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ማለት ነው፡፡
ሐ ማለት ሐመ ወሞተ በእንቲአነ ማለት ነው፡፡
ኀ ማለት ኀብአ ርእሶ ማለት ነው፡፡
ሁ ማለት ኪያሁ ተወከሉ ማለት ነው፡፡
ሑ ማለት ሰብሑ ለሥመ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኁ ማለት እኁዝ አቅርንቲሁ ማለት ነው፡፡
ሂ ማለት አስተይዎ ብሂዐ ማለት ነው፡፡
ሒ ማለት መንጽሒ ማለት ነው፡፡
ኂ ማለት ዘልማዱ ኂሩት ማለት ነው፡፡
ሃ ማለት ሃሌ ሉያ ማለት ነው፡፡
ሓ ማለት መፍቀሬ ንስሓ ማለት ነው፡፡
ኃ ማለት ኃያል በኃይሉ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሄ ማለት በኵለሄ ሀሎ ማለት ነው፡፡
ሔ ማለት ሔት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኄ ማለት ኄር እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ህ ማለት ህልው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሕ ማለት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኅ ማለት ኅብስት ለርኁባን ማለት ነው፡፡
ሆ ማለት ኦሆ ይቤ ወመጽአ ማለት ነው፡፡
ሖ ማለት ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኆ ማለት ኆኅተ ገነት ወልድ ማለት ነው፡፡
ኈ ማለት ኈለቈ አዕፅምትየ ማለት ነው፡፡
ኋ ማለት ሰንኋቲ ሥጋ ሰብእ ማለት ነው፡፡
ኌ ማለት ይኌልቍ አሥዕርተ ማለት ነው፡፡
ኊ ማለት በኊበኊ ሥጋ አዳም ማለት ነው፡፡
ኍ ማለት ዑጽፍት ወኍብርት ማለት ነው፡፡
ለ ማለት ለብሰ ሥጋ ዚአነ ማለት ነው፡፡
ሉ ማለት ሣህሉ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሊ ማለት ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ላ ማለት ላሜድ ልዑል እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሌ ማለት መቅለሌ ዕጹብ ማለት ነው፡፡
ል ማለት መስቀል ዘወልደ አብ ማለት ነው፡፡
ሎ ማለት ዘሀሎ እምቅድም ማለት ነው፡፡
መ ማለት መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሙ ማለት ሙፃአ ሕግ ማለት ነው፡፡
ሚ ማለት ዓለመ ኀታሚ ማለት ነው፡፡
ማ ማለት ፌማ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ሜ ማለት ሜም ምዑዝ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ም ማለት አምላከ ሰላም ማለት ነው፡፡
ሞ ማለት ሞተ በሥጋ ማለት ነው፡፡
ሰ ማለት ሰብአ ኮነ ከማነ ማለት ነው፡፡
ሠ ማለት ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ማለት ነው፡፡
ሱ ማለት ፋሲልያሱ ማለት ነው፡፡
ሡ ማለት መንበረ ንግሡ ማለት ነው፡፡
ሲ ማለት ዘይሴሲ ለኲሉ ዘሥጋ ማለት ነው፡፡
ሢ ማለት ሢመተ መላእክት ማለት ነው፡፡
ሳ ማለት ሳምኬት ስቡሕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሣ ማለት ሣህል ወርትዕ ማለት ነው፡፡
ሴ ማለት ለባሴ ሥጋ ማለት ነው፡፡
ሤ ማለት ሤሞሙ ለካህናት ማለት ነው፡፡
ስ ማለት ልብስ ለዕሩቃን ማለት ነው፡፡
ሥ ማለት ንጉሥ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሶ ማለት መርሶ ለአሕማር ማለት ነው፡፡
ሦ ማለት አንገሦ ለአዳም ማለት ነው፡፡
ረ ማለት ረግዓ ሰማይ ወምድር በጥበቡ ማለት ነው፡፡
ሩ ማለት በኵሩ ለአብ ማለት ነው፡፡
ሪ ማለት ዘይሰሪ አበሳ ማለት ነው፡፡
ራ ማለት ጌራ መድኃኒት ማለት ነው፡፡
ሬ ማለት ሬስ ርኡስ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ር ማለት ርግብ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ሮ ማለት ፈጠሮ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ቀ ማለት ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል ወውእቱ ቃል ኀበ
እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቁ ማለት ጽድቁ ለኃጥእ ማለት ነው፡፡
ቂ ማለት ፈራቂሁ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ቃ ማለት ቃልየ አጽምዕ ማለት ነው፡፡
ቄ ማለት ሰዋቄ ኃጥአን ማለት ነው፡፡
ቅ ማለት ጻድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቆ ማለት ቆፍ ቅሩብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቈ ማለት ተኈለቈ ምስለ ጊጉያን ማለት ነው፡፡
ቊ ማለት ቊርባነ ወንጌል ማለት ነው፡፡
ቍ ማለት ቍየጺሁ አዕማደ ባላቅ ማለት ነው፡፡
ቌ ማለት ቀነተ ሐቌሁ ለኀጺበ እግረ አርዳኢሁ ማለት ነው፡፡
በ ማለት በትሕትናሁ ወረደ ለቤዛ ኵሉ ዓለም ማለት ነው፡፡
ቡ ማለት ጥበቡ ለአብ ማለት ነው፡፡
ቢ ማለት ረቢ ነአምን ብከ ማለት ነው፡፡
ባ ማለት ባዕድ እምአምአማልክተ ሐሰት ማለት ነው፡፡
ቤ ማለት ቤት ባዕል እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ብ ማለት ብርሃነ ቅዱሳን ፍጹማን ማለት ነው፡፡
ቦ ማለት አልቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌሁ ማለት ነው፡፡
ተ ማለት ተሰብአ ወተሠገወ እማርያም እምቅድስት
ድንግል ማለት ነው፡፡
ቱ ማለት መዝራዕቱ ለአብ ማለት ነው፡፡
ቲ ማለት ተአኳቲ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ታ ማለት ታው ትጉህ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቴ ማለት ከሣቴ ብርሃን ማለት ነው፡፡
ት ማለት ትፍሥሕት ወሐሤት ማለት ነው፡፡
ቶ ማለት ነአምን ልደቶ ለክርስቶስ ማለት ነው፡፡
ነ ማለት ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ማለት ነው፡፡
ኑ ማለት ዛኅኑ ለባሕር ማለት ነው፡፡
ኒ ማለት ኰናኒ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ና ማለት መና እስራኤል ማለት ነው፡፡
ኔ ማለት ወጣኔ ኵሉ ማለት ነው፡፡
ን ማለት መኰንን እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኖ ማለት ኖላዊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
አ ማለት አአኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዐ ማለት ዐቢይ እግዚአብሔር ወብዙኅ አኮቴቱ ማለት ነው፡፡
ኡ ማለት ሙጻኡ ለቃል ማለት ነው፡፡
ዑ ማለት ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኢ ማለት ለሊሁ ተንሣኢ ወለሊሁ አንሣኢ ማለት ነው፡፡
ዒ ማለት ለሊሁ ሠዋዒ ወለሊሁ ተሠዋዒ ማለት ነው፡፡
ኣ ማለት ኣሌፍ ፈጣሬ ኵሉ ዓለም ቀዳማይ ወደኃራዊ ማለት ነው፡፡
ዓ ማለት ዓይነ ኵሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ ማለት ነው፡፡
ኤ ማለት አምጻኤ ዓለማት ማለት ነው፡፡
ዔ ማለት ዔ ዐቢይ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
እ ማለት እግዚአብሔር እግዚእ ማለት ነው፡፡
ዕ ማለት ብፁዕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኦ ማለት እግዚኦ ማለት ነው፡፡
ዖ ማለት ሞዖ ለሞት ወተንሥአ ማለት ነው፡፡
ከ ማለት ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኩ ማለት ዐርኩ ለመርዓዊ ማለት ነው፡፡
ኪ ማለት ኪያሁ ንሰብክ ማለት ነው፡፡
ካ ማለት ካፍ ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኬ ማለት ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማእከለ አኃው ማለት ነው፡፡
ክ ማለት ክብሮሙ ለመላእክት ማለት ነው፡፡
ኮ ማለት ዘረዳእኮ ለአብርሃም ማለት ነው፡፡
ኳ ማለት ኳሄላ አይሁድ ወልድ ማለት ነው፡፡
ኰ ማለት ኰናኔ ዓለም ማለት ነው፡፡
ኵ ማለት ኵርጓኔ ቅዱሳን ማለት ነው፡፡
ኲ ማለት ኲናተ ጌዴዎን ዘቈልቈለ ላዕለ ስሳ ምዕት ሐራ
በምዕር ማለት ነው፡፡
ኴ ማለት ወይኴንን እምባሕር እስከ ባሕር ማለት ነው፡፡
ወ ማለት ወረደ እምሰማያት ማለት ነው፡፡
ዉ ማለት ጼዉ ለምድር ማለት ነው፡፡
ዊ ማለት ናዝራዊ ሐዊ ማለት ነው፡፡
ዋ ማለት ዋው ዋሕድ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዌ ማለት ዜናዌ ትፍሥሕት ማለት ነው፡፡
ው ማለት ሥግው ቃል ማለት ነው፡፡
ዎ ማለት ቤዘዎ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ዘ ማለት ዘኲሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዙ ማለት ምርጒዙ ለሐንካሳ ማለት ነው፡፡
ዚ ማለት ናዛዚ ማለት ነው፡፡
ዛ ማለት ዛይ ዝኲር እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *